ስልጠናው ቀጥሏል
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለነባር የሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ማነቃቂያ ስልጠና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀጥሏል።
ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ )
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ታህሳስ7/2017 ዓ.ም ያስጀመረው የመነቃቅያ ግንዛቤ ማስጨ በጫ መረሃ ግብር ዛሬም ለአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮች እየሰጠ ይገኛል።
ለመነቃቂያ የተዘጋጀውን የንድፈ ሃሳብ ስልጠና የሰጡት የዘርፉ ባለሙያ አቶ ውድነህ አቢ እና የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት ም/ዲቪዚዮን ሃላፊ ኮማንደር መቅደስ ተስፋዬ ናቸው።
የስልጠናው አላማ የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የክ/ከተማውን ብሎም የከተማውን ሰላም እንዲጠብቅ እንድሁም የከተማው ነዋሪ የሰላም ባለቤት ማድረግና የሰላም ጉዳይ ላይ ማሳተፍ መሆኑ ገልፀዋል።
ስልጠናው በዋናነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ፣ አሰራር ስልጣንና ሀላፊነት ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 140/2014 ዓ.ም በሥነ ምግባርና እንዲሁም በወንጀል መከላከልና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሁለቱም አሰልጣኞች ዝርዝር ማብራርያ ሰጥተዋል።
መድረኩን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ከልሌ እና የዘርፉ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር ወ/ሮ ፍሬሕይዎት በለጠ ሲሆኑ በዚህ ወቅት አቶ ሳሙኤል እንደተናገሩት የሠላም ሰራዊቱ ከተማዋን ከሰላም ዕጦትችግር ለመታደግ ቀንና ለሊት የአከባቢውን ሰላም የሚጠብቅ ነውና መነቃቃት እንደሚገባ ጠቁመው በስራ ቦታ ላይ መታወቂያ እና የደምብ ልብስ መልበስ እንደሚገባ፣ በስነምግባር ላይ በጣም ትኩረት መስጠት እና ከፊታችን የሚከበሩ የተለያዩ በዓላት በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ ለማድረግ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀትና መረጃ በመለዋወጥ አብሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ሥልጠናው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት ም/ቢሮ ሃላፊ ኮማንደር መቅደስ ተስፋዬ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታየጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ከልሌ፣ የዘርፉ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር ወ/ሮ ፍረህዌት በለጠ እና ነባር የሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮች ተገኝተዋል።
ነገና ከነገ ወዲያ የአካል ብቃትና የተግባርስልጠና በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።