ቢሮው በቅንጅታዊ አሰራር እና ምርጥ ተሞክሮ ቅመ...

image description
- recent news   

ቢሮው በቅንጅታዊ አሰራር እና ምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ቢሮው በቅንጅታዊ አሰራር እና ምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም ( አዲስ አበባ )

                   ********

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለማዕከል ሰራተኞች እና የጋራ መግባቢያ የትስስር  ሰነድ ከተፈራረማቸው የባለድርሻ አካላት  በቅንጅታዊ አሰራር  እና ምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። 

መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር እንደተናገሩት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ስራ በአንድ ተቋም ብቻ መስራት የማይቻል በመሆኑ በቅንጅታዊ አሰራራችንም  ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመስራት ወንጀልንም በመቀነስ ውጤታማ ሆነናል ብለዋል። አክለውም አሁንም የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ያሉብንን ክፍተቶች በመለየትና  ተቀናጅተን በመስራት የከተማችንን ሰላም ዘላቂ ለማረጋገጥ ነው ብለዋል። 

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት የክትትልና ድጋፍ ዘርፍ የቅንጅታዊ አሰራር ቡድን አስተባባሪ  የሆኑት አቶ መታሰቢያ አየለ የስልጠናው አላማ ተቋማት  የተቀላጠፈ  ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር ግንዛቤን በማስጨበጥና አቅም በማጎልበት የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ መሆኑን ገልፀው የቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊነት፣ የቅንጅታዊ አሰራር ፅንሰ ሃሳብ፣ ጠቅሜታ፣ ስርዓት፣ የቅንጅታዊና የትብብር እሴቶች፣
እንዲሁም  የምርጥ ተሞክሮ ፅንሰሃሳብ፣ የምርጥ ተሞክሮ አይነቶችና የመለያ መስፈርት ወዘተ...ዙሪያ በዝርዝር አብራርተዋል። 

መድረኩን የመሩት የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ሲሆኑ  ሰፊውን ህብረተሰብ የሰላም ባለቤት በማድረግ ሂደት ውስጥ የቅንጅታዊ ስራ ዋና ስለሆነ ይህንኑ በማጠናከር የከተማችን ሰላምና ደህንነት አጠናክረን መጠበቅ  አለብን ብለዋል።