በወቅታዊ የከተማው የሰላም፣ የጸጥታና የደህንነት...

image description
- recent news   

በወቅታዊ የከተማው የሰላም፣ የጸጥታና የደህንነት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ ።

በወቅታዊ የከተማው የሰላም፣ የጸጥታና የደህንነት ሁኔታ  ላይ ውይይት ተካሄደ ።

             ታህሳስ 14/ 2017 (አዲስ አበባ )

                          *******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማው  ወቅታዊ የሰላም፣  የጸጥታና የደህንነት ሁኔታን በተመለከተ  ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር የሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

ውይይቱ ባለፈው ጊዜ ተመሳሳይ ውይይትና አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን አፈፃፀሙ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለመገምገም ነው ተብሏል።

በውይይቱ ላይ የሁሉም ክፍለ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች የየክፍለ ከተማቸውን አሁናዊ የፀጥታና ደህንነት ሁኔታን በተመለከተ ሪፖርት በማቅረብ ውይይት ተደርጎ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።

የቢሮው ም/ል ኃላፊዎች ከዘርፋቸው የሥራ ባህሪ አንፃር በቀጣይ መደረግ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች ላይ ዘርዘር ያሉ አስተያየቶችን  ሰጥተዋል።

ውይይቱን የመሩት የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ባስቀመጡት አቅጣጫ፣ለኮሪደር ልማት ዕንቅፋት እየሆኑ ያሉ ሁኔታዎችን መፍትሔ መስጠት፣አዲስ የሰላም ሠራዊት አባላት ምልመላ፣ሥልጠናና ስምሪት ሥራን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ክብርት የቢሮ ኃላፊዋ አክለውም መጪውን የጥምቀት በዓል ቅድመ ዝግጅትን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል፣የኑሮ ውድነትና የገበያማረጋጋት ሥራን አጠናክሮማስቀጠል፣የማሕብረሰብ አቀፍ 
ፖሊስ ማዕከላት ሁሌ ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ፣ማሕብረተሰብ አቀፍ የውይይት መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ፈጣን የመረጃ ልውውጥ፣የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓትን ማሳደግ ያስፈልጋል።

በመጨረሻም የፀጉረ ልውጥ፣የሽብርና የፅንፈኛ ኃይሎች ሁኔታ አዝማሚያን መረጃ መሰብሰብ፣
መተንተን፣ መተንበይ፣ጥብቅ ጥናት  ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የከተማውን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ
ሠጥተዋል።