
Start Date
icon
End Date
icon
Location
ከተማ አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ
ፕሬስ ሪሊዝ
ህዳር 30/2017 ዓ.ም
******
የአዲስ አአበባ ሰላምና ፀጥታአስተዳደር ቢሮ ከተማ አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው ።
" ሀገር ወዳድነትና የሀገረ መንግስት ግንባታ" በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የግንባር ቀደም ሚናቸውን ይወጡ ዘንድ የተዘጋጀ ኮንፈረንስ መሆኑን የቢሮዉ ም /ኃላፊ አቶ ተሰፋዬ ጫኔ ገልፀዋል።
እንደምክትል ቢሮ ሃላፊዉ ገለፃ የሰላም ኮንፈረንሱ በ 119 ወረዳዎች ነገ ማለትም ማክሰኞ እና በ 11ዱም ክ/ ከተሞች ደግሞ ሀሙስ በአንድ ቀን ይካሄዳል ብለዋል።
የኮንፈረንሱን ተሳታፊዎች በተመለከተ
በየወረዳው 500 እና በየክፍለ ከተማው 1000 ተሳታፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን በጠቅላላዉ እንደ ከተማ ከ80,000 በላይ ህዝብ ይሳተፋል ብለዋል።
ኮንፈረንሱን ከነገ ታህሳስ 1/2017 ዓ. ም ጀምሮ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸዉን ም/ቢሮ ኃላፊዉ ተናግረዋል ።