Events

Events የቅርብ ጊዜ ሁነቶች

image description
Start Date icon
End Date icon
Location በሁሉም ክ/ከተሞች

ፕሬስ ሪሊዝ

"የእምነት ተቋማት ለሰላም ግንባታና ለልማት ያላቸው ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከተማ አቀፍ ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነዉ ።

ታህሳስ 13/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት ጉዳዮችና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ "የእምነት ተቋማት ለሰላም ግንባታና ለልማት ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ ኮንፈረስ ሊካሄድ እንደሆነ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ እንደገለፁት የኮንፈረንሱ ዓላማ በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ያሉ አመራሮችና አስተዳደሮች ከተማው ላይ በሚካሄደው የሰላም ግንባታና የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያላቸውን ሚና ትልቅ ስለሆነ እሱን በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል ።

ሀላፊው አያይዘውም መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ፤ ኃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ቢባልም ነገር ግን በከተማው ልማትና ሰላም ዙሪያ በጋራ ለመስራት ያለንን ፍላጎት ለማሳየትና የዕምነት ተቋማት በከተማው ላይ የሰፈነውን ሰላም ለማስቀጠል ሚናቸው ከፍተኛ ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

የእምነት ተቋማትና ህብረተሰቡ በቀጣይም በከተማው ላይ የሚካሄዱ የአደባባይም ሆነ የአዳራሽ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማድረግ የተዘጋጀ ኮንፈረንስ መሆኑን ሀላፊው ገልጸዋል፡፡

ኮንፈረንሱ በዛሬው ዕለት በከተማው ውስጥ ባሉ በሁሉም ወረዳዎች፤

በነገው ዕለት ደግሞ በሁሉም ክ/ከተሞችና እንዲሁም የማጠቃለያው መርሃ- ግብር ደግሞ በከተማ ደረጃ በቀጣይ ሳምንት እንደሚካሄድ ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

መረጃው፡- የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡