
Start Date
icon
End Date
icon
Location
11ክፍለ ከተማ
4ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት ስልጠና ሊጀመር ነው
ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
******
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ስተዳደር ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት 4ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት ስልጠና ሊጀመር ነው::
ስልጠናው ከነገ ሚያዝያ 16 ቀን ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለአስር ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የንድፈ ሃሳብና የመስክ ወታደራዊ ስልጠና እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ገልፀዋል፡፡
ም/ቢሮ ኃላፊው አክለውም የሰላም ሰራዊት አባላት ምልመላ፤ስልጠናና ስምሪት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የማድረጊያ አንዱ መንገድ መሆኑን ጠቅሰው በያዝነው በጀት ዓመት ስልጠና ሲሰጥ ይህ 3ኛው ዙር መሆኑን ተናግረው በዚህ ዙር አስራ አንድ ሺ ሰልጣኞች እንደሚከታተሉ ገልፀዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም ለክፍለ ከተማ አስተበባሪዎችና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን መሰጠቱን ጨምረው ገልፀዋል፡፡